የጾም ሕግጋት

የጾም ሕግጋት፦5
ታላቁ የረመዷን ወር ነፍስ ራሷን ከምግብ እንደዚሁም ከተለያዩ መጥፎ ቦታ የምታርቅበት የተባረከ ወር ሲሆን አንዳንዶች ግን ከዚህ በኋላ የምግብ አይነቶች አይበሉም የተባሉ ነው የሚመስሉት። ጾመው ውለው ለሚያፈጥሩበትን ለማዘጋጀት ከስሁር ይጀምራሉ፤ ምግብን ማነስ የረመዷንን በረካ ያበዛል። አላህ ያግራልን
 [ስለ ረመዷን የሚያብራራ ከክፍል አራት የቀጠለ]፦ጾመኛ ሆኖ ተኝቶ ኢሕቲላም (የዘር ፈሳሽ የወጣበት) የሆነ ጾሙ አይበላሽም። በመርሳት ሳይሆን አውቆ በመተሻሸት ወይም በእጁ የዘር ፈሳሹ እንዲወጣ ካደረገ ግን ጾሙ ይበላሻል። በቀን (ሌሊት ሳይሆን) ጾመኛነቱን እያስታወሰ ፍርዱንም ሐራም መሆኑን እያወቀ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመ የዘር ፈሳሽ ባይወጣም ጾሙ ይበላሻል። በመርሳት ወይም ባለማወቅ ከሆነ ግን ቀዷእ የለበትም። በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በሌላ ምክንያት ከእንቅልፍ ሲነቃ ጀናባ ከሆነ ወይም የዘር ፈሳሽ ወቶት ሆኖ ራሱን ያገኘ ቀኑን ይጾማል።ለሶላት ይታጠባል። ለጾም ግን ትጥበት አያስፈልገውም። ምክንያቱም ትጥበት የሲያም ቅድመ ሁኔታ አይደለም።

እናታችን ዓኢሻ ረድየሏሁ ዐንሃ ሲናገሩ፦
كَانَ رَسُولُ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسلَّم:"يُدْرِكُهُ الْفَجْرُ وَهُوَ جُنُبٌ مِنْ أَهْلِهِ ثُمَّ يَغْتَسِلُ وَيَصُومُ" رواه البخاريُّ

ትርጉም፦ ★«የአላህ መልዕክተኛ❤♥️ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሚስቶቻቸው ጁኑብ ሆነው ፈጅር ገብቶባቸው ታጥበው ይጾሙ ነበር»★ብለዋል። ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ አውቆ በምላስ ድልጭታ  ሳይሆን ኩፍር ላይ መውደቅ ይገኝበታል። ይኸውም ሳይገደድ በምርጫው በቀልድም ሆነ በንዴት ጾመኛነቱን ቢያስታውስም ባያስታውስም ነው። ምክንያቱም የካፊር ዒባዳ ታባይነት የለውምና። ስለዚህም ከሶስቱም የኩፍር ዓይነቶች መጠንቀቅ እና በነርሱም ላይ በጭራሽ ላለመውደቅ ራስን መጠበቅ የግድ ይላል።
እነዚህ ሶስቱ የኩፍር አይነቶችም ዝርዝራቸው፦ 
①,የንግግር_ኩፍር፦አላህን መሳደብ እስልምናን መሳደብ የመሳሰሉት፣
 ②,*የእምነት_ኩፍር፦አላህን አካል፣ ብርሃንና መንፈስ ነው ብሎ በልብ ማመን፣
   ③,የድርጊት_ኩፍር፦ቁርዓንን ቆሻሻ ስፍራ መጣል፣ ለጣዖት መስገድ እና ሌሎችም የመሳሰሉት ናቸው።
ማሳሰቢያ፦አንዳንድ ሰዎች "ነሚማ" (ሰዎችን ለማጣላት ነገርን ማመላለስ፣ ማማት፣ መዋሸት፣ ተቃራኒ ጾታን በስሜት ማየትና መሳም ጾምን ያበላሻል ማለታቸው ትክክል አይደለም።
   ነገር ግን ከነዚህ ውስጥ አንዱን እንደ ነሚማ ያሉት የጾምን ምንዳ ያሳጣሉ። ሐራምም ናቸው። ስለዚህ ጾመኛ ሙስሊም ምላሱን ከመጥፎ ንግግሮች እንደ ውሸት፣ማማትና ሙስሊምን የሚጎዱ ንግግሮችን ከመናገር መጠበቅ አለበት። አንድ ሰው የሰደበው እንደሆነ እኔጾመኛነኝ ይበል። እንደዚሁም የረመዷን ወር ነፍስን የማፅጃ ወር እንጂ መብልና መጠጥ የሚያበዙበት ወር እንዳልሆነ ልናውቅ ይገባል። ሐሳቡ መብላትና መጠጣት ብቻ የሆነ ሰው በአኺራ ትልቅ ደረጃን ከሚያገኙት አይሆንም።
    አላህ በሰማነው ተጠቃሚ ያድርገን!! አሚንን

Please publish modules in offcanvas position.

web tasarim ucuz web sitesi siteni yukarı çıkar istanbul web tasarım İnternet Reklam hizmetleri uygun web tasarımcı uygun web sitesi seo hizmetleri