ጾምንየሚያበላሹነገሮች

بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله الصلاة والسلام على رسول الله،
ጾምንየሚያበላሹነገሮች
አላሁ ተዓላ ትዕዛዝን በዋጅብነት ሲያዘን አያይዞም የሚከለከሉትንና የሚፈቀዱትን አውርዶልናል። ስለ ረመዷን የሚያብራራ ከክፍል ሶስት የቀጠለ፦አንድ ሰው እንደ ጣቱ ያለን ነገር ወደ አፉ አስገብቶ እያወቀ ያስታወከ፣ ከትውከቱ ወደ ሆዱ የተመለሰ ነገር ባይኖርም ጾሙ ይበላሻል። በሐዲስም ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም
قَالَ رَسولْ الله صَلى الله عَلَيْهِ وَسلم:مَنْ ذَرَعَهُ الْقَيْءُ ـ أَيْ غَلَبَهُ ـ وَهُوَ صَائِمٌ فَلَيْسَ عَلَيْهِ قَضَاءٌ وَمَنِ اسْتَقاءَ فَلْيَقْضِ" رواهُ الحَاكَمُ والأَربعَةُ
ትርጉም፦ «ፆመኛ ሆኖ ትውከት ያሸነፈው ቀዷእ የለበትም። አውቆ ያስታወከ ግን ቀዷእ ያውጣ»ብለዋል። እንደዚሁም «በቀን ከግብረ ስጋ ግንኙነትና፣ የዘር ፈሳሽን በእጅና በመተሻሸት ከማውጣት መቆጠብ ግዴታ ነው»ምክንያቱም ጾምን ያበላሻሉና።
   ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች!!
የሰሊጥ ፍሬ የምታክል ወይም ከሷም የምታንስ፣ ጾመኛ መሆኑን እያስታወሰ ፍርዱንም (ሐራም መሆኑን) #እያወቀ መብላት። እንደዚሁም ጠብታ ውኃ ወይም መድሃኒትም ቢሆን መጠጣት ጾምን ያበላሻል።
ማሳሰቢያ ፦የመንገድ ላይ አዋራ ወይም የዱቄት ብናኝ መከላከሉ አስቸጋሪ በመሆኑ ጾምን አይጎዱም። ምግብን መቅመስ እስካልዋጡት ድረስ ጾምን አይጎዳም። ከልክ በላይ አፍን በውኃ በመጉመጥመጥ ውኃው ወደ ሆድ ከገባ እና በአፍንጫ ዉኃን በመሳብ ውኃው የአፍንጫን ወሰን ያለፈ እንደሆነ ጾሙ ይበላሻል።
ምራቅ ከአፍ እስከ ውጨኛው የከንፈር ክፍል ከመጣ በኋላ መልሶ ከተዋጠ ጾሙ ይበላሻል። ነገር ግን ከምላስ እስካልተለየ ድረስ ቢዋጥም ጾሙን አይጎዳም። አክታም ጉሮሮን አልፎ ላንቃ ላይ ከደረሰ በኋላ እንደገና ተመልሶ ቢዋጥ ጾሙ ይበላሻል። ኢማም አቡ ሐኒፋ ዘንድ አክታ ምላስ ድረስ ደርሶም ቢዋጥ ጾምን አያበላሽም። አንድ ሰው ትውከት አሸንፎት አስታውኮ ትውከቱ ከቆመለት በኋላ አፍን ሳያጠራ ምራቁን ከዋጠ ጾሙ ይበላሻል። ምክንያቱም ምራቁ አፉ በደረሰው ትውከት ስለተበላሸ ነው። ሲጋራ የሚያጨስ ሰው አጠገብ የተቀመጠ ጾመኛ ለምሳሌ፦(መኪና ውስጥ)የሲጃራው ጪስ ወደ አፉ ገብቶ ሆዱ ቢደርስም ጾሙን አያበላሽበትም።
የእጣን ጭስና ሽቶን ማሽተት ጾምን አያበላሽም። ነገር ግን ሲጋራውን የሚያጨስ ሰው ጾሙ ይበላሻል። ምክንያቱም ከሲጋራው ተለይተው የሚወጡ ትናንሽ ብናኞች ወደ አጫሹ (ተጠቃሚው ሰው) ሆድ ስለሚደርሱ ነው። የጆሮና የአፍንጫ ጠብታ ጾምን ያበላሻል። በብልት የሚሰጥ መድሃኒትም ጾምን ያበላሻል። ነገር ግን መርፌ ቆዳ ላይ ወይም ደምስር ላይ መወጋት ጾምን አያበላሽም። ምክንያቱም ቆዳ ከክፍት አካሎች ስለማይመደብ።በጾም ቀን እራሱን ስቶ የነቃ ሰው ራሱን መሳቱ ሙሉ ቀን እስካልወሰደበት ድረስ ጾሙ አይበላሽም። ራሱን መሳቱ ከፈጅር እስከ ፀሐይ መጥለቅ የቆየ ከሆነ ግን ጾሙ ይበላሻል። እብደት ከሆነ ግን ለአንድ አፍታም ቢከሰት ጾሙን ያበላሻል። እንደዚሁም የወር አበባም ሆነ የኒፋስ (የወሊድ) ደም በሴት ልጅ ላይ ከመጣ ፀሐይ ልትጠልቅ ትንሽ ቢቀራትም ጾምን ያበላሻል።
     አላህ በሰማነው ተጠቃሚ ያድርገን!!አሚንን

Please publish modules in offcanvas position.

web tasarim ucuz web sitesi siteni yukarı çıkar istanbul web tasarım İnternet Reklam hizmetleri uygun web tasarımcı uygun web sitesi seo hizmetleri