የጾም_ግዴታዎች

የጾም_ግዴታዎች
بسم الله الرحمن الرحيم
 الحمد لله الصلاة والسلام على رسول الله,
የጾም ሕግጋት፦ ክፍል3
አላሁ ተዓላ የሰው ልጆችን በአንዳች ነገር ላይ ሲያዝ ከገደብ፣ ሸርጥና ግዴታዎች ጋር ያዘናል። የጾም ግዴታዎች ሁለት ናቸው። እነሱም፦
አንደኛው፦ንያ ማድረግ ሲሆን ስፍራዋም ልብ ነው። ከአንደበት ማውጣቱ ግዴታ አይደለም። ለእያንዳንዱ የረመዷን ቀን ኒያን ሌሊት መድረግ ግዴታ ነው። ጾም ያለ ኒያ ትክክል አይሆንም። መደረግ ያለበትም ከማፍጠሪያ ሰዐት ጀምሮ ፈጅር እስኪመጣ ድረስ ባለው ጊዜ ነው።በልቡ
نَوَيْتُ صِيَامَ يَومِ غَدٍ مِن شَهرِ رَمَضَان.
ነወይቱ ሲያመ የውሚ ገ’ዲን ሚን ሸህሪ ረመዷን ይላል።ትርጉሙም፦ «ከረመዷን ወር የሆነውን የነገውን እለት ለመፆም ኒያ አድርጊያለሁ።»ይህ በሻፊዒይ መዝሀብ ሲሆን በሌሎች ዘንድ በመጀመሪያው ሌሊት ለረመዷን ቀናቶች በሙሉ መነየት ይቻላል። በልቡም
"نَوَيتُ صِيَام ثَلاثِينَ يَومًا عَن شَهرِ رَمَضَانَ هَذِهِ السَّنَة"
‘‘‘ነወይቱ ሲያመ ሰላሲነ የውመን ዓን ሸህሪ ረመዷን ሃዚሂ ሰና’’’ይላል።ትርጉም «የዚህን አመት የረመዷን ወርን ሰላሳውን ቀን ለመፆም ኒያ አድርጊያለሁ»ይላል።ኒያ ሌሊት ማድረግ ግዴታ የሚሆነው በፈርድ ጾም ጊዜ ሲሆን የሱና ጾም ከሆነ ግን የዝሁር ሶላት ወቅት ከመግባቱ በፊት ባለው ጊዜ ኒያ ማድረግ ይችላል።
የወር አበባ ወይም ኒፋስ (የወሊድ) ደም በጾም ሌሊት ያቋረጠላት ሴት ባትታጠብም ቀጣዩን ቀን ለመጾም መነየት አለባት።ምክንያቱም ትጥበት ለሶላት እንጂ ለጾም ትክክለኛነት ቅድመ ሁኔታ (ሸርጥ) አይደለምና።ኒያ ካደረጉ በኋላ መብላት፣መተኛትና የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ከፈጅር በፊት እስከሆነ ድረስ ጾሙን አይጎዳውም።በሻፊዒይ መዝሀብ ሌሊት ኒያ ሳያደርግ ተኝቶ ከፈጅር በኋላ የነቃ ሰው ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች ታቅቦ መዋልና ቀዷእ መክፈል ይኖርበታል።
ሁለተኛል፦ኢምሳክ(መቆጠብ)፦ሲሆን ከፈጅር እስከ መግሪብ (የፀሐይ መጥለቅ) ባለው ጊዜ መብልና መጠጥ እንደዚሁም ማንኛውንም መጠን ያለው ነገር ትንሽም ቢሆን ክፍተት ባለው አካል እንደ አፍና አፍንጫ እንደዚሁም በሽንትና ሰገራ መውጫ በኩል ወደ ራስ፣ሆድና አንጀት ውስጥ ከመግባት መቆጠብ ማለት ነው።በመርሳት የበላ ወይም የጠጣ ሰው ብዙም ቢሆን ጾሙን አያበላሽበትም። በሱና ጾምም ቢሆን። በሶሒህ ሐዲስ እንደተዘገበው ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም፦
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:"مَنْ نَسِىَ وَهُوَ صَائِمٌ فَأَكَلَ أو‌ْ شَرِبَ فَلْيُتِمَّ صَـوْمَهُ فَإِنَّمَا أَطْعَمَهُ اللهُ وَسَقَاه"رواه البخارِيّ
ትርጉም፦"ጾመኛ መሆኑን በመርሳት የበላ ወይም የጠጣ ጾሙን ያጠናቅ (ይጨርስ) ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና ብለዋል። ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል።አላህ በሰማነው ተጠቃሚ ያድርገን!!አሚንን

Please publish modules in offcanvas position.

web tasarim ucuz web sitesi siteni yukarı çıkar istanbul web tasarım İnternet Reklam hizmetleri uygun web tasarımcı uygun web sitesi seo hizmetleri