አህለን ቢከ ያ!ረመዷን

አህለን ቢከ ያ!ረመዷን
بسم الله الرحمٰن الرحيم
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله
 የጾም_ሕግጋት፦
قال الله تعالى:يَأَيُّهَا الََّذِين ءَامَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُُّون
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዛ ከናተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ እንደተፃፈው ሁሉ በናተም ላይ ታዟል ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።28:183
የረመዷንን ወር በመፆም ማሳለፍ የማንኛውም የአቅመ አዳም /አቅመ ሔዋን ግዴታ ነው። የተባረከው ረመዷን ወር ጾም ታላቅ ዒባዳ ከመሆኑም ባሻገር አላሁ ተዓላ በልዩ ልዩ ነገሮች ልዩ አድርጎታል። ከነዚህም ውስጥ አላህ በሐዲስ አል―ቁድሲይ እንዲህ ይለናል፦
قال تعالى:كُلُّ حَسَنَةٍ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلى سَبْعِمٍائَةِ ضِعْفٍ إِلاَّ الصيَام،فَإنَّهُ لِى وَأَنَا أَجْزِى بِهِ" رواه الْبخاري
ሁሉም ጥሩ ስራዎች በአስር እጥፍ እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ይባዛሉ ጾም ሲቀር! ጾም ለኔ ነው። /ምንዳውን እኔ ነኝ የምሰጠው" ቡኻሪይ ዘግበውታል።ፍጡራኖች ዒባዳን የሚያደርጉት ለአንድ አላህ ብቻ ሲሆን ጥቅሙም ለራስ ነው።የጾምን ምንዳ ልኩን የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ ማለት ነው።
የረመዷንን ወር መጾም ግዴታ የሆነው በሒጅራ አቆጣጠር በሁለተኛው ዓመተ ሒጅራ ላይ ነው።ነብያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ረመዷኖችን ጾመው ነበር ወደ አኺራ የሄዱት። ይህን የተከበረ የረመዷንን ጾም መጾም ዓሊሙም ጃሒሉም  የሚያውቀውና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ምንም አይነት ተቃውሞ የማይነሳበት ታላቅ የዒባዳ ዘርፍ ነው።በመሆኑም ግዴታነቱን ያስተባበለ ሰው ለእስልምና አዲስ ወይም ዑለማኦች ከሚገኙበት ቦታ ርቆ ያደገ ካልሆነ ውጭ ከእስልምና ይወጣል።
ነገር ግን ግዴታ መሆኑን እያመነ ያለ ምንም ምክንያት ያፈጠረ ከሆነ ኃጢያተኛ ይሆናል እንጂ በዚህ ተግባሩ ብቻ አይከፍርም።ያፈጠራቸውንም ቀናት ቀዷእ ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል።
የተባረከውን የረመዷን ወር መጾም ግዴታ ለመሆኑ ማስረጃ ከዑለሞች ስምምነት (ከኢጅማዕ) በፊት የሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ነው።
قال الله سبحانه وتعالى: "كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَام" سورة البقرة 
ትርጉም፦ጾም ግዴታ ሁኖባችኋል። ነብያችንም❤ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "بني الإسلام على خمسٍ شهادة أن لا إله إلا اللهُ وأنَّ محمدًا رسول الله،وإقام الصلاة،وإيتاءِ الزَّكاة،وحجَّ البيْتِ وصَوم رمضان،"رواه البخاري ومسلم
«እስልምና የተገነባው በአምስት ነገሮች ነው። እነሱም፦ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚገዙት አምላክ እንደሌለና ነቡዩ ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ሶላትን ቀጥ አድርጎ መስገድ፣ዘካትን  ማውጣት፣ሐጅ ማድረግና የረመዷንን ወር መጾም ናቸው» ብለዋል ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል። አላህ በሰማነው ተጠቃሚ ያድርገን!!አሚንን

Please publish modules in offcanvas position.

web tasarim ucuz web sitesi siteni yukarı çıkar istanbul web tasarım İnternet Reklam hizmetleri uygun web tasarımcı uygun web sitesi seo hizmetleri